ወግ ፍለጋ ወደ ትውስታ ማሕደሬ ስገባ የተለያዩ መረጃዎችን የያዙ ሦስት ዓይነት ፎልደሮች አገኛለሁ፡፡ ጎልማሳነት፣ ወጣትነት እና ልጅነት
˝ጎልማሳነት” የሚለው ጥቁር ፎልደር ገለጥ ሳደርገው፣ የሐሳብ ብዛት እንደ ብረት አለሎ የሚከበድ ጭንቅላት ያሸከመው ጭንቀታም ሽማግሌ የላባ ትራስ ላይ ተኝቶ ጊዜውን፣ መንግሥቱን፣ አገሪቱን፣ ትውልዱን፣ ኑሮውን… ይራገማል፡፡
“ወጣትነት” የሚለው ቀይ ፎልደር ስከፍተው በስሜት የሚቃትት ፍም ማንነት እንቅልፍና እረፍት አጥቶ ቡና ቤት ደጃፍ ይልከሰከሳል፡፡ የሴት ወገብ አንቆ ያለከልካል፡፡ ያጨሳል፡፡ ያስታውካል፡፡ ይጨማለቃል፡፡
“ልጅነት” የሚል ሥያሜ ከተሰጠው ነጭ ፎልደር ውስጥ ስገባ ደግሞ የቀን ጨዋታ ያደከመው ብላቴና አጎዛ የተነጠፈበት ቀጠላ ላይ ያለምንም ትራስ “ጧ” ብሎ ተኝቷል፡፡ (ላባው ትራሴ ሳይሆን እራሴ ነበርኩ፡፡)
*
ኢትዮጵያዊ ነን!
የጦቢያን፥ የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ
በልባችን ውስጥ አትመን፥ ታላቅነቷን የምንተርክ
ከኑቢያ እስከ ኢትዮጵያ፥ ከኤሌክትሮን እስከ ሳባ
የነገሥታቶቻችንን ገድል፥ ታሪካቸውን ሳናዛባ
ጀብዷቸውን የምንተርክ፥ ሥማቸውን የምናውስ
አክናሁስ፣ ካልንሶ፣ ኢትዮጲስ፣ ሰኑካ፣ ቦኑ፣ አሩአሳ፣ ጲኦሪ፣ አክቲሳኒስ፣ ማንዱስ፣
…ጵሮቶውስ፣ አንጋቦስ፣ ዘግዱር፣ ሔርሔቶር፣ ሑርሖር፣ ጲያንኪያ፣ ዴውስ፣
…አጼ ዳዊት፣ ልብነ–ድንግል፣ ገላውዲዮስ፣ ሱስኒዮስ
…ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒልክ፣ ዘውድቱ፣ ኢያሱ፣ ኃይለ ስላሴ፣ መንግሥቱ፣ መለስ
በጎም አደረጉ ክፉ፣ ነገን ያክል ቀን እያለ ትናንትን ዛሬ የማንከስ……… ኢትዮጵያዊ ነን፡፡
**
[image error]
አማልክቱ ዓሣዎችን በባሕር፣ ሰዎችን ደግሞ በአየር ውስጥ እንዲንኖር ፈጠሩን፡፡ ለአእዋፍቶች ክንፍን፣ ለዓሣዎች ጊልስን፣ ለሰዎች እግርን… ቸሩን፡፡ ግን ሰው እንደ እራሱ ፍቃድ አንዳንድ ነገሮችን ያደርግ ዘንዳ ተፈቅዶለታል፡፡ ለምሳሌ ያህል እንደ ፍላጎታችን በውኃ እና በሕዋ ላይ እንዲንንሳፈፍ ይሁንታን ተችሮናል፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን አንዳንድ የተፈጥሮ ስጦታዎች አሉ በተለምዷዊ መንገድ በማሰባችን የተነሳ ማድረግ የማንችላቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሁሉም ሬሳዎች መንሳፈፍ ይችላሉ፡፡ ሁሉም ሰዎች ግን መንሳፈፍ አይችሉም፡፡ አንድ ዋና የማያውቅ ሰው በሕይወቱ እያለ ዉሃ ያዘለ ባሕር ውስጥ ቢገባ እራሱን ለማዳን ቢጥርም የመንሳፈፍ ጥበብ መዝናናትን እንጂ ማሰብን የማይጠይቅ በመሆኑ መዋኘት ሳይሆን አካሉን ማዝናናት አቅቶት ሰምጦ ይሞታል፡፡ ከክብደታችን በላይ ሐሳባችን ተጭኖን እንዘቅጣለን፡፡
መጽሐፉን ለመግዛት (ለማዘዝ) ከታች ይጫኑ። 
Published on October 17, 2020 13:26